የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ቦይንግ ሠር የሆኑና ለእስራኤል ሊላኩ የነበሩ መሣሪያዎችን እንዲዘገይ አድርጓል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አራት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል ...
በአሜሪካ በመካከለኛው ምዕራብ በኩል ባሉ ግዛቶች ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ ትላንት ተከስቶ በርካታ ውድመት ማስከተሉ ታውቋል። ሚሽጋን ቀኑን በሙሉ በአውሎ ነፋስ ወይም ቶርኔዶ ስተመታ ውላለች፡፡ ...
በደቡብ አፍሪካ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ባለበት ወቅት፣ በአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የተለቀቀውና ሰንደቅ ዓላማ ሲቃጠል የሚያሳየው ማስታወቂያ “የሃገር ክህደት” ነው ሲሉ ...
(ኔቶ) ወታደሮችን ወደ ዩክሬን የሚልክ ከሆነ “እጅግ አደገኛ” ሊሆን እንደሚችል ሩሲያ ዛሬ ረቡዕ አስጠንቅቃለች፡፡ የኔቶ ወታደሮች ጣልቃ እንዲገቡ ዩክሬን ያቀረበችውን ጥያቄ ሞስኮ በቅርበት ...
የአደጋ ሰራተኞች ዛሬ ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካዋ የጆርጅ ከተማ ለበርካቶች ሞት ምክኒያት ከሆነው የሕንጻ መደርመስ አደጋ የተረፉትን ለማዳን በመሯሯጥ ላይ ናቸው። ባሉበት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ...
በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ በተመታችው ኬንያ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል። ለሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ እና በተከተለው ጎርፍ ሳቢያ ክፉኛ በተጠቃው ታና ወንዝ በተሰኘው አውራጃ አካባቢ 44 ሰዎች በኮሌራ እንደተያዙ የዓለም ...
በደቡብ አፍሪካ ከሁለት ቀናት በፊት ከተደረመሰው ሕንፃ ሥር ሰዎችን በሕይወት የማግኘት ጥረቱ ዛሬም ቀጥሏል። ተስፋ እየተመናመነ ቢሆንም፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬ ረቡዕም ፍለጋቸውን ቀጥለዋል። በደርዘን የሚቆጠሩ ሠዎች አሁንም ያልተገኙ ሲሆን፣ ሰኞ ዕለት በግንባታ ላይ የነበረው ሕንፃ ሲደረመስ ሰባት ሰዎች ...
ሺ በአውሮፓ የሚያደርጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት ለመጀመር ፈረንሳይ ገብተዋል የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ትላንት ሰኞ በኤሊዜ ቤተ መንግስት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ነው ‘ከፈረንሳይ ጋር አዲስ የትብብር ግንኙነት ለመጀመር መፍቀዳቸውን’ የተናገሩት። “አሁን በሚታየው ...
የገዥው ፓርቲ ቃል አቀባይ ጊልበርት ባዋራ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል "ቶጎዊያን በግልፅ ደግፈውናል" ብለዋል። ምዕራብ አፍሪካዊቱን ሃገር ለአርባ ዓመታት የገዙትን አባታቸውን ኢያዴማን የተኩት ...
የኦለምፒክ ሯጩ ኢትዮጵያዊ አትሌት ጠና ነገሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በማራቶን ውድድር ዝናን ካተረፉ አትሌቶች አንዱ የኾነው የኦሎምፒክ ሯጩ አትሌት ጠና ነገሪ፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ...
የፋሲካ በዓልን በተለያየ ዐውድ እና ስሜት እንደሚያከብሩ፣ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ የአሜሪካ ድምፅ በመቐለ፣ ባሕር ዳር፣ ሐዋሳ እና አዲስ አበባ ከተሞች ያናገራቸው ኢትዮጵያውያን፣ የዘንድሮውን ፋሲካ ከወትሮው በተለየ ስሜት እንደሚያከብሩት ገልጸዋል፡ ...
የተባበሩት መንግስታት የኒዩክሌር ቁጥጥር ተቋም ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ እየተፋጠነ ባለው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የኒውክሊየር መርሃ ግብር ላይ ተቋማቸው የሚያደርገውን ቁጥጥር ለማሻሻል ዛሬ ሰኞ ወደ ...